ቴሌግራፍ

ከውክፔዲያ


ቴሌግራፍ የመልእክት ግኑኝነት - በማተሚያ መሳሪያ የሚዘጋጅ የፅሁፍ ህትመት ቀደም ሲል ዋና የመገናኛ መንገድ ነበር፡፡ ቀጥሎም ቴሌግራፍ (telegraph) ፈጣን ግኑኝነትን ወደ ሩቅ ስፍራ ለማድረስ አስቻለ፡፡ የራዲዮ ስርጭት መጀመር የቴሌግራፍን ዝና ቀነሰው፡፡ ሽቦ አልባ ቴሌግራፍ ብሎም ስልክ የአንድ ለአንድ ቀጥታ ግኑኝነትን እስከ መፍጠር ደረጃ ላይ ደረሰ፡፡ የቴሌቪዥን መስኮት ዋናው የብዙኃን መገናኛ የግኑኝነት መንገድ ሆነ፡፡ ዘመነ ኢንተርኔት ቴሌግራፊክ ወይንም የመልእክት ግንኙነትን በሽቦ አልባ ዘዴና አጠቃቀሙ ጎልብቶ እና ቀሎ በመምጣቱ እነ ጋዜጣ፣ ራዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ስልክን በመጠቅለል ላይ ይገኛል።

የቴሌግራፍ ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቴልግራፍ ማለት (በግሪክ ቋንቋ «ቴሌ» ማለት ከርቀት፤ «ገራፋይን» ማለት መፃፍ) ማለት ሲሆን፤ የረዥም ርቀት የፅሁፍ ወይንም የመልእክት ማስተላለፍን የሚወክል ነው፡፡ ይህም መልእክቱን የሚሸከም ወይንም የሚያደርስ አካልን አያካትትም፡፡ የኤኬክትሪክ ቴሌግራፍ የኤሌክትሪክ ሲግናልን በተዘጋጀ የሽቦ መስመር ወይንም በራዲዮ ሞገድ መልክ መላክን ይገልጻል፡፡ ይህም አዲስ የተገኘውን የኤሌክትሪክሲቲ ክስተት ማለትም ኃይሉን ማምረትና መቆጣጠር ሲቻል አብረው ያሉትንም እንደ የኬሚካል ለውጦች ብልጭታዎቹን የማይለዋወጡ ቻርጆች የስበት ሀይል፤ የኤሌክትሪክ ንዝረት እና የማግኔቲዝም ጠባዩ ላይ ምርምር እና ክትትል ሲቀጥል ነው፡፡https://encrypted-tbn3.gstatic.com/images?q=tbn:ANd9GcQtUx3iBGn6_ozQy3I_108cikKSH33dFCnefKinvtsnuLpIoYNbQw


የቴሌግራፍ አይነቶች እና ዕድገቱ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ·        በጀርመኖቹ ፊዚሺያኖች የኤሌክትሮኬሚካል ቴሌግራፍ ዘዴ የሚጠቀመው በአንድ ወገን ብዙ ሽቦዎች እያንዳንዳቸው ልዩ የሆነ ስም ወይንም ፊደል የሚወክሉ አንድ በአንድ በኤሌክትሪክ ቻርጅ ሲደረጉ በሌላኛው በኩል እነዚህ ሽቦዎች ጫፋቸው የኬሚካል እቃ ውስጥ ተነክረው ቻርጅ በተደረገው ሽቦ መስመር ያለው ኬሚካል በሚፈጥረው እንፋሎት መሰል ምልክት ወይንም በብል ትርጉም መስጠትን ያመለክታል፡፡ ·        ዴቪስ ሪሌይ (Davy's relay) በመበል የሚታወቀውም ትንሽ ከረንት ፍሰት ትልቅ የኤሌክትሮማግኔት እንቅስቃሴን በማስነሳቱ ይህም የኤሌክትሪክ ሲግገናል ማስተላለፍ ወይንም ቴሌግራፍ፤ የኤሌክትሮማግኔትም መታወቅ እናም ጥቅል ሽቦዎችን በማብዛት ኢንሱሌትድ በሆነ ብረት ዙሪያ የሚፈጠረውን የማግኔቲክ ኃይል ከፍ ማድረግ፣ ሳይንቲስቱ ሃንስ ክርስቲያን አረስትድ (Hans Christian Ørsted) እ.ኤ.አ.በ1820 ዓ.ም የኤሌክትሪክ ዥረት የማግኔቲዝም ኃይል እንደሚፈጥር እና ይህም የደቡባዊ ዋልታ የሚያመለክት አመልካችን እንደሚያንቀሳቅስ፤ ቀጥሎም ጆሐን ሽቫይገር (Johann Schweigger) የተባለው ጋልቫኖሜትር ወይንም የኤሌክትሪክ ዙረትን ፍሰት አመልካች መሳሪያ በመፈልሰፉ፤ አንድሬ-ማሪ አምፔር (André-Marie Ampère) ጋልቫኖሜትሮችን በማሰባሰብ ልክ እንደ ኤሌክትሮኬሚካሎቹ በእያንዳንዱ ሽቦ ላይ የሚመጣውን የኤሌክትሪክ ፍሰት በማመልከት የቴሌግራፍ ጥቅም እንደሚገኝ አመልክቷል፡፡https://encrypted-tbn1.gstatic.com/images?q=tbn:ANd9GcRIDb_x285wRWpDz7Vc_28EbBFmRywyiQ-epQvvdAcOu2Gn8XZB
  • ሳሙኤል ሞርስ (Samuel Morse) የሞርስ ኮድም (Morse code) ·        የሚባለውን ለእያንዳንዱ ፊደሎች የተለየ ድምፅ በመቀጠል በቴሌግራፍ ታዋቂ ነው፡፡ https://encrypted-tbn1.gstatic.com/images?q=tbn:ANd9GcTHmQd_XwE9zO-btSYzLn4KCsnDHestcjXCLWUz9GSqmy0LGeYAjw
  • የኤፍ. ጋውስ (F. Gauss) ጋልቫኖሜትርም በዘዴው ተሻሽሎ ኮሚውታቶር በመጠቀም፤ ከቮልታይክ ፒል ወይንም ከባትሪ መሰል ይልቅ የኢንዳክሽን የኤሌክትሪክ ኃይል (ፐልስ) በማድረግ በኮሚውታቶሩ አማካኝነት የዙረት አመልካች ቀስቷን በፖዘቲቭ እና በኔጌቲቭ አቅጣጫ በማንቀሳቀስ በዚሁ ኮድ የተሰጠውን ፊደሎች ማስተላለፍ መቻሉ ሲሆን እነዚህ ፖዘቲቭ እና ኔጋቲቭ መጠኖችም ሊገኙ የቻሉት ጥቅል ሽቦዎችን በማግኔቱ ዙሪያ ወደ ላይ እና ወደታች በማንቀሳቀስ ነበር፡፡ በዚህም ሰባት 7 ፊደሎችን በደቂቃ ማስተላለፍ ተችሎ ነበር፡፡ https://encrypted-tbn0.gstatic.com/images?q=tbn:ANd9GcQqRGgOC513Scn4JjgzyjQnP6MEC2LAFgAC_gRgVcQeHxbRSdd0
  • የቻርልስ ዊትሰቶን (Charles Wheatstone) ቴሌግራፍ አመልካች ቀስትን እንደ ሰዓት ቆጣሪ ገበታ ላይ መልእክቱን እንዲያመለክት ማድረግ ነበር፡፡ ይህም የቴሌግራፍ መልእክቶችንም ከኮዳቸው ወደ ግልፅ ትርጓሜ ለማምጣት የሰለጠኑ ሰዎች ፍላጎት ያስቀረ ነበር፡፡ እንዲሁም መልእክቱ በሚመጣበት ወቅት ተርጓሚዎች መኖር ነበረባቸው፡፡ እናም በ1846 ዓ.ም አሌክሳንደር ቤን (Alexander Bain) የኬሚካል ቴሌግራፍን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ዥረት ሲግናል የብረት ጠቋሚን በወረቀት ላይ የቀለም ምልክት እንዲያደርግ በማድረግ ከዛም እነዚህን ምልክቶችንም በሌላ ጊዜ መተርጎም ያመለክታል፡፡ ቀጥሎም የፊደል ገበታ ያላቸው መሳሪያዎች (ኪ-ቦርድ) መልእክት የሚልኩ ቴሌግራፎችን በመጠቀም ፊደሎቹን ሲቀበሉ ወዲያውኑ በሞርስ ኮድ ማተም ተጀመረ፡፡ ሌላውም በሞርስ ኮዶች መሰረት የኤሌክትሪክ ሲግናሉ ሲመጣ በታመቀ አየር በመጠቀም ቀዳዳዎችን በወረቀት ላይ በመብሳት ቀጥሎም መተርጎም ይከተላል፡፡

https://encrypted-tbn2.gstatic.com/images?q=tbn:ANd9GcTlwa15YpVkaSLyipQ11ImaYmY7oXdunWqESQp-yOP46N6SoS4Xtw Archived ማርች 23, 2022 at the Wayback Machine ተግዳሮቶች

  • የሽቦዎች መጠነ አቃቢነት ወይንም ካፓሲታንስ እና ሽቦው በረዘመ ቁጥር የኃይሉ መጠን እንቅፋት ወይንም ረዚስታንስ እየጨመረ በመሄዱ የሚገኘው የመልእክት ፍጥነት ላይ ተፅእኖ አሳድሯል፡፡
  • ለዚህም ሲፎን መቀበያ "siphon receiving" የሚባል መሳሪያ በ…… የሚሰራ ፍጥነቱን ወደ 20 ፊደሎች በደቂቃ አድርሶታል፡፡
  • ኦሊቨር ሄቪሳይድ (Oliver Heaviside) የማስተላለፊያ መስመሩን የሲግናል መዛባት ለማጥፋት በሽቦው ላይ የዥረት አቃቢነት ወይንም ኢንደክታንስ ቢጨመርበት የሚለውን ሀሳብ አፈለቀ እንደዚሁም ይህ ኢንሱሌትድ ሽቦ የኤሌክትሮማግኔት ፀባዩን ከፍ በማድረግ ረዚስታንሱ የሚያመጣውን ጉድለት ቀንሶታል፡፡ ይህ ኢንሱሌተር ወይንም ኤልክትሪክ የማያስተላልፍ ፕላስቲክ መሰል ከኢሴያ ክፍለ ዓለም ከሚገኝ ዛፍ ጉታ ፐርቻ (gutta-percha) እንደሚገኝ ታውቆ በስኮትላንድ ሀኪም ታውቆ ነበር፡፡ እናም እነ ፋራዳይ ለኤሌክትሪክ ኢንሱሌተርነት እንዲውል አደረጉት፡፡
  • ሌላው የቴሌግራፍ ተግዳሮት የነበረው የመላኪያ ፍጥነቱን መጨመር ነበር (ፊደሎች/በደቂቃ) ይህም በሰው የሚሰራ እጅ ስራን ማስቀረት ይጨምራል፡፡ ለዚህም የድምፅ ሰራተኞችን መዝግቦ በመተንተን… ሞርስ ኦፐሬተር የተባለው መሳሪያ ዶት እና ዳሽ ኮዶችን በመለየት በሚጠቀመው ዘዴ………
  • ቶማስ ኤዲሰንም መልቲፕሌክ ቴሌግፍ (multiplex telegraphy) ሲግናሎችን በጊዜ በፍጥነት (Time Division Multiplexing) በመከፋፈል የሚገኘውን እስከ ቤል ቴሌፎን (A. Bell telephone) ዕያለ መሻሻል አሳይቷል፡፡

https://encrypted-tbn0.gstatic.com/images?q=tbn:ANd9GcSs23GCLFo0PXBwUHKdB7_ZA1nOVjO2ItY4R5r7gav-aRnAId_ErA

የአጠቃቀም ዕድገቱ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ጋውስ በ1835 በጀርመንባቡር መስመር ጣቢያ የቴሌግራፍ መስመር ለትግበራ ውሎ ነበር፡፡
  • በ1840 ዓ.ም ሞርስ የኤሌክትሪክ ቴሌግራፉን ለዕይታ ባቀረበበት ወቅት የተላከውን መልእክት ፈጣሪ በመጀመሪያ ምን አለ “What hath God wrought?” የሚል ትርጉም ያለው ይመስላል፡፡ እናም ለአሜሪካው ምክር ቤት በጻፈው ማስታወሻ ሞርስ እንዲህ ብሎ ነበር - ይህን መሰሉ የፈጣን ግኑኝነት መሳሪያ ትልቅ ውጤት ያለው ስለሚሆን ስለዚህም ልክ እንደ አያያዛችን ለጥሩም ለመጥፎም ሊውል ይችላል፡፡ "This mode of instantaneous communication must inevitably become an instrument of immense power, to be wielded for good or for evil, as it shall be properly or improperly directed.
  • ኮክ እና ዊትስቶን የኤሌክትሪክ ቴሌግራፍ ካምፓኒ (Electric Telegraph Company) መስርተው በ13 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ለንግድ ያዋለውን የቴሌግፍ መስመር በግሬት ዌስተርን ሬይልዌይ (Great Western Railway) አካባቢ ዘረጉ፡፡ ይህም ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሲሰጥ ነበር፡፡

https://encrypted-tbn0.gstatic.com/images?q=tbn:ANd9GcQVA8MhvnkUjZ9uNkoTB8f2NIhHOE8gi0RTbV88CgFGKyZ9-9yI-w

  • እ.ኤ.አ በ1850ዎቹ በእንግሊዝ እና በ ፈረንሳይ መካከል የቴሌግራፍ መስመር ሲዘረጋ በመጀመሪያ ባይሳካም በሁለተኛ ሙከራ ግንኙነት ማድረግ ተችሎሏል፡፡ ቀጥሎም በ1860ዎቹ አትላንቲክ ውቂያኖስን ያቋረጠ የትሌግራፍ መስመር መዘርጋት ተችሎ በአሁጉራት መካከል ያለውን የጊዜ እና የቦታ ርቀት ክብደትን ያሳጣው ሆኗል፡፡ ዌስተርን ዩኒየን የመሳሰሉ ድርጅቶች ዋና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ነበሩ፡፡ እንደዚህም እያለ በፓሲፊክ ላይ የቴሌግራፍ ግኑኝነት በ1902 ሲጠናቀቅ የብሪቲሽ የባህር ውስጥ መስመር ዝርጋታ አብዛኛውን የወከለ ነበር፡፡ የዌስተርን ዩኒየን የቴሌግራፍ ግልጋሎት እስከ 2006 ድረስ ሲሰራ የነበረ ሲሆን፤ የህንድም የቴልግራፍ አገልግሎት እስከ 2013 ድረስ ጥቅም ላይ ውሎ ነበር፡፡
  • ኮክ እና ዊትስቶን የኤሌክትሪክ ቴሌግራፍ ካምፓኒ (Electric Telegraph Company) መስርተው በ13 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ለንግድ ያዋለውን የቴሌግፍ መስመር በግሬት ዌስተርን ሬይልዌይ (Great Western Railway) አካባቢ ዘረጉ፡፡ ይህም ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሲሰጥ ነበር፡፡ ↵https://encrypted-tbn0.gstatic.com/images?q=tbn:ANd9GcQVA8MhvnkUjZ9uNkoTB8f2NIhHOE8gi0RTbV88CgFGKyZ9-9yI-w↵-➞ እ.ኤ.አ በ1850ዎቹ በእንግሊዝ እና በ ፈረንሳይ መካከል የቴሌግራፍ መስመር ሲዘረጋ በመጀመሪያ ባይሳካም በሁለተኛ ሙከራ ግንኙነት ማድረግ ተችሎሏል፡፡ ቀጥሎም በ1860ዎቹ አትላንቲክ ውቂያኖስን ያቋረጠ የትሌግራፍ መስመር መዘርጋት ተችሎ በአሁጉራት መካከል ያለውን የጊዜ እና የቦታ ርቀት ክብደትን ያሳጣው ሆኗል፡፡ ዌስተርን ዩኒየን የመሳሰሉ ድርጅቶች ዋና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ነበሩ፡፡ እንደዚህም እያለ በፓሲፊክ ላይ የቴሌግራፍ ግኑኝነት በ1902 ሲጠናቀቅ የብሪቲሽ የባህር ውስጥ መስመር ዝርጋታ አብዛኛውን የወከለ ነበር፡፡ የዌስተርን ዩኒየን የቴሌግራፍ ግልጋሎት እስከ 2006 ድረስ ሲሰራ የነበረ ሲሆን፤ የህንድም የቴልግራፍ አገልግሎት እስከ 2013 ድረስ ጥቅም ላይ ውሎ ነበር፡፡