ዋናው ገጽ/ምርጥ ፅሑፎች

ከውክፔዲያ

ምርጥ ፅሑፎች (ዕጩዎች ይምረጡ!)


ቢግ ማክሃምበርገር ዓይነት ሲሆን በፈጣን ምግብ ቤቱ ማክዶናልድስ የሚሸጥ ነው። ሃምበርገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በ1960 ዓ.ም. በአሜሪካኑ ጅም ዴልጋቲ ነበር። ሁለት የተፈጨ የበሬ ስጋ ክቦችን፣ ሰላጣ ቅጠል፣ ዓይብ፣ ሽንኩርት፣ ፒክልስ እና ሶስት የሰሊጥ ጠፍጣፋ ዳቦዎችን ከማዋዣ የቢግ ማክ ሶስ (መረቅ) ጋር ይይዛል።

ቢግ ማክ በኣሁኑ ዘመን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተዎዳጅነትን በማግኘቱ ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው የሥነ ንዋይ ጋዜጣ በያመቱ ቢግ ማክ ኤንዴክስ የተባለ መረጃ ያትማል። ቢግ ማክ በያገሩ የሚሸጥበትን ዋጋ በማዎዳደር፣ የየአገሩን የኑሮ ውድነት ለማነጻጻር ይጠቀምበታል።


ታሪክ በዛሬው ዕለት (ጁን 2, 2024 እ.ኤ.አ.)

ግንቦት ፳፭

  • ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የመጀመሪያዎቹን አራት ኢትዮጵያውያን ጳጳሳት (አቡነ አብርሓም - የጎንደር እና የጎጃም፤ አቡነ ይስሐቅ - የትግሬ እና የስሜን፤ አቡነ ጴጥሮስ የወሎ እና የላስታ፤ አቡነ ሚካኤል - የኢሉባቡር እና የምዕራብ ኢትዮጵያ) ከግብጻዊው ሊቀ ጳጳሳት (አቡነ ቄርሎስ)ጋር ካይሮ ላይ ተቀብተው ተሾሙ።
  • ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - የታላቋ ብሪታኒያ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ በዚህ ዕለት ቅብዐ ቅዱስ ተቀብተው ከአባታቸው ከንጉሥ ጊዮርጊስ ሳድሳዊ የወረሱትን ዘውድ ጫኑ። የዘውዱ ሥነ ሥርዓት በመቶ ሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የራዲዮ አድማጮች የተሠራጨ ሲሆን በታሪክ ለመጀመሪያም ጊዜ በአዲሱ የትዕይንተ መሳታዋት (television) ታይቷል።
  • ፲፱፻፴፰ ዓ/ም - የኢጣልያ ሕዝብ በጣለው የድምጽ ምርጫ የንጉዛታዊ ሥርዓትን ትቶ አገሪቱ የሪፑብሊካዊ አስተዳደር እንድትከተል አደረገ። የቀድሞው ንጉሥ ዳግማዊ ኡምቤርቶ አገር ለቅቀው ተሰደዱ።